- Started on: 26 apr 2026
- Closing Date: 16 dec 2026
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሐፍ አብረን እናሳትም
ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ከተጻፉ ሌሎች ሥራዎች በብዙ መልኩ ይለያል። በመጀመሪያ፣ ከቅድመ ክርስትና ጀምሮ እስከ አሁኑ ዘመን ድረስ ያለውንና ከሦስት ሺሕ ዓመታት ያላነሰ የታሪክ ዘመን የሚሸፍን ሲሆን፤ በኹለተኛ ደረጃ ደግሞ እስካሁን ድረስ በሌሎች መጻሕፍት ውስጥ ትኩረት ያላገኙና ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጋራ የተያያዙ ርእሰ ጉዳዮችን በጥልቀት በመዳሰሱ ነው። በሦስተኛ ደረጃ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ዙሪያ የሚነሡ የታሪክ ጥያቄዎችን በመለየት፣ ለእነርሱም በማስረጃ የተደገፈና ሚዛናዊ ምላሽ ለመስጠት ጥረት የተደረገበት ሲሆን፤ በአራተኛ ደረጃ ደግሞ “በአንድ ድንጋይ ኹለት ወፍ” እንደሚባለው፣ ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ እያነበቡ ስለ ኢትዮጵያም አጠቃላይ የታሪክ ጕዞ እግረ መንገዱን ሰፊ ግንዛቤ ያስጨብጣል። በተጨማሪም መጽሐፉ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሻገር ስለ እስልምና፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንትና ሌሎች የእምነት ተቋማት ከሀገራችን ተጨባጭ ኹኔታ አንጻርታሪካዊ ትንታኔ ይሰጣል። በመጨረሻም፣ እነዚህን ሐሳቦች ለማጠናከር እጅግ በርካታ የዋቢ መጻሕፍትና የግርጌ ማስታወሻዎች ጥቅም ላይ መዋላቸው ሥራውን ይበልጥ አስተማማኝ ያደርገዋል።
ይህን መጽሐፍ ያዘጋጁት ቀሲስ መንግሥቱ ጎበዜ (ዶ/ር) በማስተማር፣ በምርምርና በቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የረጅም ጊዜ ልምድ የአላቸው ባለሞያ ናቸው። ከዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርኪኦሎጂና የቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል የማስተማር ልምድ ጀምሮ፣ በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (በፍሎረንስ ከተማ የጣልያን ሕዳሴ ጥናት ማእከል) በምርምር ቆይታ፣ በስዊድን የደብረ መዊዕ ሉንድ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ክህነታዊ አገልግሎት እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳንና በሰንበት ትምህርት ቤቶች ጉልህ ተሳትፎ አድርገዋል።
ይህ መጽሐፍ ለታሪክ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች፣ ለሰንበት ትምህርት ቤትና ለነገረ መለኮት ተማሪዎች፣ ለቤተክርስቲያን መምህራንና በአጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን የታሪክ ጕዞ ለማወቅ ለሚፈልጉ አንባብያን ሁሉ በቂ ግንዛቤ የሚሰጥ ነው።
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር አሳታሚ እና አከፋፋይ ሲሆን ይህን መጽሐፍ በወገንፈንድ ላይ ቀድመው ለእርሶ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሰንበት ትምህርት ቤት፣ የአብነት ትምህርት ቤት ፣ ለትምህርት ተቋማት በስጦታ ቀድመው በመግዛት መስጠት ይችላሉ።
የመጽሐፉ ገጽ ብዛት: 650
ዋጋ: 1600 ብር
Copyright 2026 - Wegenfund | Powered by WegenTech