የዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነምህረት ማህበረ ደናግል የእናቶች አንድነት ገዳም

cause-image
  • Started by: Emahoy Askalemariam Samuel
  • For: EOTC_logo
  • Started on: 16 may 2026
  • Closing Date: 16 sep 2026

የዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነምህረት ማህበረ ደናግል የእናቶች አንድነት ገዳም ያለበትን የፅኑ መጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት የታለመው አዲስ የውሃ ፕሮጀክት ሥራ እንዲጀመር፣ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የምትገኙ ምእመናን በጎ ልገሳ እና ድጋፍ አሁን ላይ እጅግ አስፈላጊ ሆኗል።

ይህንን የእናቶቻችንን የረጅም ጊዜ የመጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚነሳውን ታላቅ ፕሮጀክት አስጀምሮ ዳር ለማድረስ፣ ኮሜዲያን እሸቱ በዶንኪ ቲዩብ (Donkey Tube) ላይ አሁን ገዳሙ ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የእናቶቻችንን ፈተና እና የውሃ ፕሮጀክቱን አስፈላጊነት የሚያሳይ ልዩ ዶክመንትሪ ይዞ ቀርቧል።

ይህንኑ ዶክመንትሪ እያያችሁ፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች እና በጎ አድራጊዎች ሁሉ ይህ ወሳኝ የውሃ ፕሮጀክት በተሳካ ሁኔታ ሥራውን እንዲጀምርና ግቡን እንዲመታ የምትችሉትን ሁሉ እንድትረዱን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 1,335,456 of ETB 10,924,675 12%