- Started by: Kune Demelash
- For: Gelila St George
- Started on: 05 oct 2026
- Closing Date: 05 jan 2027
"... ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤“ ት.ኢሳ 61:3
በደቡብ ኢትዮጰያ በደቡብ ኦሞ ና አሪ ዞኖቸ ሀገረ ስብከት ስሜን አሪ ወረዳ ቤተክህነት የገሊላ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የካቲት 30/2013 ከ6 ዓመት በፊት በደረሰበት ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ህንፃ መቅደሱ እና ነዋዬተ ቅዱሳት ከጥንታዊ የብራና መዛግብት ጋር ተቃጥሏል። በእግዚአብሔር ቸርነት እና ረድኤት ታቦታቱን ከመቅደሱ ያለአንዳች ጉዳት ቢተርፉም ማረፍያ በማጣታቸው የተነሳ የቆርቆሮ መጋዝን ውስጥ ለጊዜው እንዲቀመጡ ተደርጓል።
ይህችን የተቃጠለችውን ቤተክርስቲያን መልሶ እንደገና በመገንባት አገልግሎት እንዲሰጥባት ለማድረግ በቁጥር ጥቂት የሆኑ የአከባቢ ኦርቶዶክሳውያን ካላቸው ላይ ቀን ሰው በመስጠት በታላቅ ቁጭት ህንፃ መቅደሱን ከ2013 ጀምሮ ለ6 ዓመታት ለመገንባት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ለመጨረሻ የአቅም ማነስ ያለ በመሆኑ የተነሳ ታቦተ ጊዮርጊስ እና ታቦተ ገብርኤል በቆርቆሮ በተሰራ ጊዚያዊ አዳራሽ እስከዛሬ ድረስ እንዲቆዩ ሆኗል።
አሁን ላይ በአከባቢ ምዕመናንን ጥረት ብቻ የህንፃ መቅደሱ ከፊል የስትራክቸራል ሥራው አልቆ አጠቃላይ ቀሪ የፊኒሺንግ እና የግንባታ ሥራዎች ለማጠናቀቅ ት ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል።
የአካባቢው ምዕመን በቁጥር ጥቂት ከመሆኑም በላይ ይህን አሟልቶ ታቦታቱ በተዋበ መቅደስ ለመመለስ የአቅሙም ውስንነት ፈተና ሆኖባችዋል። ስለሆነም በገንዘብና በማቴሪያል ድጋፍ በማሰባሰብ የህንጻ ቤተክርሲያኑን ግንባታ ፍጻሜ በጉጉት ለሚጠባበቀው ለገሊላና ለአካባቢው ሕዝብ መሻቱ እንዲፈጸም ድጋፍ እናድርግ።
Copyright 2026 - Wegenfund | Powered by WegenTech