ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት - " ትውልድ ምሳሌ ይፈልጋል "

project-image
  • Started by: Michu Bet
  • For: photo_2022-10-20_23-14-47.jpg
  • Started on: 25 may 2026
  • Closing Date: 30 sep 2026

" ትውልድ ምሳሌ ይፈልጋል "

ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት በሀገራችን በዓይነቱ ልዩ የሆነ እና ከእያንዳንዱ ሰው ጀርባ ያሉት ወላጆች፣ ልጆች እና ባለውለታዎች የሚመሰገኑበት የሽልማት ሥነ ሥርዓት ነው። ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት

ይህ የሽልማት ሥነ ሥርዓት በምቹ ቤት ሚዲያ እና ኢቨንት ለሦስተኛ ጊዜ የሚከናወን ነው።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተሸለሙት በርካታ ለቤተሰብ ምሳሌ ብቁ ከሆኑ ተሸላሚዎች መካከል የ 103 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋዋ ( በ 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ያረፉ ) እማሆይ ዋሪቱ ጭሮ ይገኙበታል።

ይህ የሽልማት መርሐ ግብር ለሁላችን ጥያቄ የሆነብንን እንደ ቤተሰብ ብሎም እንደ ሀገር "ለምን " ? እንዲህ " ሆን " ? ለምን እንዲህ አልሆነም ? ማን ይህንን ያድርግ ? ይህ የማን ሥራ ነው ? እና ወዘተ እያልን ለምንጠይቀው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ ትውልድንም አባት፣ እናት፣ ልጅ፣ ወንድም፣ እህት፣ አጎት ፣ አክስት እና ባለውለታ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው።
ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት

፩ ለሀገር ምሳሌ የሚሆን ሰው ከጀርባው ወላጅ እና ዘመድ አዝማድ ዋጋ ያልከፈለለት የለም። እነዚህን ዋጋ ከፋዮች ዘወትር ከልብ እናመስግናለን ። በሕብረት ሆነን ይህንን ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማትን እናዘጋጅ።

እርስዎ የዚህ ታሪካዊ እና ፫ኛ
ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት ሸላሚም አመስጋኝም እንዲሆኑ እና ድጋፍ እንዲያደርጉ በክብር ጋብዘንዎታል ።

" መሠረት ሳይጥል ቤት የሚሠራ
ማን ነው ?
ቤተሰብ የሀገር መሠረት ነው። "

አዘጋጅ :- ምቹ ቤት ሚዲያና ኢቨንት

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 10,769 of ETB 200,000 5%