- Legal Name: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት
- Fundraising Since: 09 may 2023
- Website: eotc-nw.org
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በክልሉ ከሚገኙ አህጉረ ስብከት አንዱ ሲሆን የዋግ ሕምራ ሀገረ ስብከትን ጨምሮ ራሱን ችሎ ጽ/ቤት ከፍቶ ከተዋቀረበት ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ ለ33 ዓመታት ያህል አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል። በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ውስጥ 1482 ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 27 የአንድነት ገዳማት፣ 27 በሰበካ ጉባኤ የሚተዳደሩ ገዳማት፣ 465 አድባራት እና 963 የገጠር አብያተ hርስቲያናት ናቸው። ከነዚህም ውስጥ የጎብኝን ትኩረት የሚስቡ የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ ከ116 በላይ ውቅር፣ ፍልፍልና የዋሻ ውስጥ ኪነ-ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናትና ታሪካዊ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
Whatever you choose, thank you!
Copyright 2024 - Wegenfund | Powered by WegenTech