EOTC_logo

ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት አርሴማ

  • Legal Name: ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት አርሴማ
  • Fundraising Since: 01 apr 2026
  • Registraition number: 1135692018

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በለሚ ኩራ ክፍለከተማ ሰሚት ኮንደሚኒየም አካባቢ የሚገኘው የሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት አርሴማ አዲሱ ካቴድራል ከታህሳስ 6 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በግንባታ ላይ ይገኛል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምዕመናን ባሉበት አካባቢ አሁን ያለው ቤተክርስቲያን ግን የመያዝ አቅሙ ከመቶ ሺህ በታች በመሆኑ ህጻናት እና አረጋዊያን ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል በፀሀይ እና በዝናብ ደጅ ላይ ረጅም ሰልፍ እንዲሰለፉ ተገደው ይገኛል። ይህ አዲሱ ካቴድራል ይህን ችግር ከመቅረፍ ባሻገር ለቀጣይ ብዙ መቶ ዓመታት ካህናት እና መዘምራን ሰዓታቱን፣ ማህሌቱን እና ሌላውንም መንፈሳዊ አገልግሎት በምቾት ለምዕመናን እንዲያቀርቡ ያስችላል።

በአሁኑ ሰዓት የህንጻው ተክለቁመና (Structure) ያለቀ ሲሆን ቀሪ የማጠናቀቅ (Finishing) ስራዎችን ማለትም የጥርብ ድንጋይ ማንጠፍ፣ የእንጨት እና የብረት በሮች፣ መስኮቶች፣ ቅዱሳት ስዕላት፣ መንበሮች፣ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና ሌሎችም ጎን ለጎን የሚሰሩ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ስራዎችን እያከናወንን እንገኛለን።

ከላይ ለተዘረዘሩት ስራዎች በዚህ ዓመት ወደ መቶ አስር ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገንዝበናል። የአካባቢው ምዕመናን ያለ የሌለ አቅማቸውን አሟጠው እዚህ አድርሰውታል። ቀሪውን ስራ ለመጨረስ በመላው ዓለም የምትገኙ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቅድስት አርሴማ ወዳጆችን ከበረከቱ እንድትሳተፉ ለመጋበዝ ተገደናል።

ስለሆነም አነሰ በዛ ሳትሉ ይህን ህንጻ ለፍጻሜ እንድናበቃው እና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሚያዝያ 23 ቀን 2019 ዓም ቅዳሴ ቤቱን እንድናከብር በሕያው እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን። አምላከ ቅዱሳን ትንሽ ለግሰን ታላቅ በረከትን ለማግኘት ያብቃን።

Recent Causes

Please, help us to help others

    Ways you can support us

  1. You can simply use the Donate to Semitgiyorgis button above and we will apply the funds to any of the causes as we see fit.
  2. Alternatively, you can select a cause that appeals to you more, and give as generously as you can. And, don't forget to inform others, too.
  3. Finally, to go the extra-mile, you can Start a new cause to fundraise from your friends and family.

Whatever you choose, thank you!

Image