eotc-logo-original-2

ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም

  • Legal Name: ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም
  • Fundraising Since: 03 jul 2025
  • Registraition number: 1057201

"በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ ወደ ቀደመ ክብሩ እንመልሰው"

ጥንታዊውና የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ በመባል የሚታወቀው ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም፣ የዕውቀትና የጥበብ ማእከል፣ የሊቃውንት መፍለቂያ፣ የድርሰትና የትርጓሜ ከፍተኛ ጉባኤ ቤት፣ የአሠረ ምንኵስና አስኬማ መላእክት መገኛ ነው፡፡ ቅዱስ አቡነ ሰላማ የባረኩት፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳሙን የመሠረቱትና ያሳደጉት፣ አቡነ ተክለሃይማኖት የመነኰሱበት፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተማሩበት፣ የእነ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፣ የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ የአቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የአቡነ ሠረቀ ብርሃን፣ የአቡነ በግዑ፣ የአቡነ ብስጣውሮስ እና አእላፍ ጻድቃን በረከትና ቃልኪዳን መካነ ጽድቅ፣ የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የቅኔና የሥነ ጽሑፍ፣ የትርጓሜ፣ የሥነ ጥበብ፣ የዜማና የቅዳሴ ሁለንተናዊ የዕውቀት ምሰሶ፣ መዝገበ አእምሮ፣ መካነ ቅርስ፣ ባህረ ጥበብ፣ ፍኖተ አሚንና የእምነት ምስክር ነው።

ያለማቋረጥ ከ1400 ዓመታት በላይ ተጠብቆ የቆየውን ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ ለመላው ዓለም ማስተዋወቅ ስለሚገባ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ ወደ ቀደመ ክብሩ እንመልሰው በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 27 እስከ 29 እዚያው ከገዳሙ በቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ ይደረጋል። የዚህ የበረከት ተካፍይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

Recent Causes

Please, help us to help others

    Ways you can support us

  1. You can simply use the Donate to hayk estifanos button above and we will apply the funds to any of the causes as we see fit.
  2. Alternatively, you can select a cause that appeals to you more, and give as generously as you can. And, don't forget to inform others, too.
  3. Finally, to go the extra-mile, you can Start a new cause to fundraise from your friends and family.

Whatever you choose, thank you!

Image