- Legal Name: Fanos Lehulu Charity Organization
- Fundraising Since: 06 aug 2026
- Registraition number: 5389
- Phone: +251939203402
- Email: fanoslehulucharityo…
- Website: fanoslehulu.com/
Fanos Lehulu Charity Organization
ፋኖስ ለሁሉ የበጎ አድራጎት ድርጅት (Fanos Lehulu Charity Organization, FLCO) በዋናነት በሁለት በጎ አድራጎት ድርጅቶች በጎ ሃሳብ፤ስምምነትና ትብብር ማለትም ፋኖስ በጎ አድራጎት ማህበር እና ደላንታ ተራድዖ ማህበር ቅንጅት የተመሰረተ ነው፡፡ ድርጅቱ “ፋኖስ” የሚለውን ስያሜ የተሸከመው ብርሃን እና ተስፋን በማመሳከር ሲሆን “ለሁሉ” የሚለው ደግሞ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የመስጠት አላማውን ያመላክታል። ድርጅቱ በበጎ ፈቃደኞች፣ በለጋሾች እና በ አባላቱ ትብብር የተለያዩ የልማት እና የሰብአዊ እርዳታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ፋኖስ ለሁሉ የበጎ አድራጎት ድርጅት (FLCO) በኢትዮጵያ ሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በመሆን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት የካቲት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ህጋዊ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተቀብሏል፡፡ FLCO ሀገር አቀፍ ድርጅት ቢሆንም በቂ አቅምና አደረጃጀት እስኪኖረው ድረስ በደላንታ ወረዳ እና አካበቢው ሥራውን በማካሄድ ጀምሯል፡፡
ድርጅቱ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በአካባቢ ጥበቃና ልማት ዘርፍ የበጎ አድራጎት ስራ ለመስራት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ለሚሰሩት የበጎ አድራጎት ስራዎች ፍኖተ-ካርታ እቅድ በማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
2.1. ተልዕኮ
አባላቱን በማስተባበር ድርጅቱ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች በሚደረጉ የልማት፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ሁለንተናዊ የማህበረሰብ ለውጥ በማምጣት ዘላቂ የማህበረሰብ ልማት በተዋሃዱ የትምህርት፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ማጎልበቻ ፕሮግራሞች አማካኝነት መፍጠር ነው።
2.2. ራዕይ
ፋኖስ ለሁሉ የበጎ አድራጎት ድርጅት የተለወጠች የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማየት ይናፍቃል፤ በተለይም ወላጅ አልባ ሕጻናት፣ እንዲሁም ተጋላጭ የሆኑ ወገኖች እና በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ሴቶችና አረጋውያን ትኩረት የሚሰጣቸው ሲሆኑ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ ለጤና፣ ለትምህርት እና ለኢኮኖሚ ማጎልበቻ ተደራሽነት ያለው ማህበረሰብ እንዲሆን ማድረግ ነው።
2.3. እሴቶች
• ርህራሄ (Compassion)፦ ለምንደግፋቸው ሁሉ ብሩህ የወደፊት ጊዜ መንገድ መክፈት፣ በተለይም ወላጅ አልባ ሕጻናት፣ ተጋላጭ ልጆች እና በድህነት ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ላይ ትኩረት በማድረግ በርህራሄ ማገልገል።
• ታማኝነት (Integrity)፦ ሁልጊዜ በሐቀኝነት፣ በሥነ-ምግባር፣ በአስተማማኝነት እና በመተማመን የተሞላ ባህሪ በማሳየት የህብረተሰቡን ችግሮች ለመቅረፍ እንተጋለን።
• ግልጽነት (Transparency): የገንዘብ አጠቃቀምን፣ የፕሮጀክት ሂደቶችንና ውጤቶችን ለማህበረሰቡና ለሚመለከታቸው አካላት በግልጽ በማሳወቅ እንሰራለን።
• ቶሎ መላመድ (Agility): እንደየሁኔታው የድርጅቱን ስራዎች እና ስልቶች በፍጥነት ከወቅታዊው የማህበረሰብ ፍላጎት ጋር ማጣጣም።
• ማህበረሰባዊ ኃላፊነት (Social Responsibility)፦ የምንደግፋቸው ግለሰቦች ሕይወታቸው እንዲለወጥ እና የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች በአዎንታዊ መልኩ እንዲለወጡ ለመመስከር በሃላፊነት እንሰራለን።
3. ዓላማ
• የማህበረሰባችን የኢኮኖሚ አቅም ሊያሻሽሉ የሚችሉ አማራጮችን በጋራ በማፈላለግና ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ደጋፊ በማፈላለግ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር ቅንጅት በመፈጠር የማህበረሰባችን የኢኮኖሚ አቅም ማሻሻል፡፡
• ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች በቂ ድጋፍ በማድረግ የትምህርት ውጤታማነት ማሻሻል፡፡
• የአካባቢና የተፈጥሮ ሀብት መራቆት በማህበረሰባችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስና መከላከል ብሎም ዘርፉ በሙያና በገንዘብ በመደገፍ ምርታማ ማድረግ ፡፡
• የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ላይ ሁለገብ ድጋፍ ማድረግ፡፡
• ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አረጋውያን፣ ሴቶችና ህጻናትን በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ፡፡
Whatever you choose, thank you!
Copyright 2026 - Wegenfund | Powered by WegenTech