eotc-logo-original-2

Menbere Lue Kidus Markos Kudus Michael

  • Legal Name: Menbere Lue Kidus Markos Kudus Michael
  • Fundraising Since: 22 aug 2025

የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተው በ፲፱፲፮(1916) ዓ.ም በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ነው። ቤተ ክርስቲያኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው በአዲስ አበባ ከፍተኛ ፲፩(11) ክልል ውስጥ በቀድሞው ገነተ ልዑል ቤተ መንግስት በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ በስተምዕራብ ቀድሞ እቴጌ መነን አሁን ደግሞ የካቲት ፲፪(12) በሚባለው ትምህርት ቤት በስተደቡብ ባለው ቦታ ላይ ነበር። በዚያን ጊዜ ተሰርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን አነስ ያለ ቢሆንም እጅግ በጣም ያምር እንደነበረ ወህይወተ ሥጋ ያሉ አባቶች ይናገራሉ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ቤተ ክርስቲያን ለ፲(10) ዓመታት ያህል ካገለገለ በሇላ ደጃዝማች ወንድይራድ የተባሉ አባት ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ቤተ ክርስቲያኑ አሁን ካለበት ቦታ ላይ ተዛውሮ እንዲሰራ በ፲፱፻፳፭(1925) ዓ.ም ጥያቄ ቀርቦ በንጉሡ ተጠንቶ ትክክለኛነቱ ስለታመነበት በደጃዝማቹ ገበዝነት (ኃላፊነት) በንጉሡ ገንዘብ አሁን ያለው ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ተጀመረ።በ ፲፱፻፳፮ ዓ.ም ሥራው ተጠቃሎ ጳጳሳት በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ቤተ ክርስቲያኑ አገልግሎት መሥጠት ከጀመረ ጀምሮ ለ ፬ ጊዜ ያህል እድሳት ተደርጎለታል።
ቤተ ክርስቲያኑ በቤተ መንግስት ውስጥ የተተከለበት ፪ ዐበይት ምክንያቶች አሉት።

፩ኛው፦ ንጉሡ ገና የንግስና መዕረግ ሳይሰጣቸው በሐረር ክፍለ ሃገር በሚገኘውና አረማያ ተብሎ ይጠራ በነበረው ባህር(ሐይቅ) በጉዞ ላይ እንዳሉ ጀልባዋ አደጋ ደረሰባት። በዚያም ጊዜ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጉዳት ሳይደርስባቸው ዳኑ። ቀኑ የቅዱስ ማርቆስ መታሰቢያ እለት ሰለነበረ ከዚህ መከራ በዕለተ ማርቆስ በመዳናቸው ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ ታቦተ ማርቆስን በቅጽረ ቤተ መንግስታቸው ውሰጥ እንዲተከል አድርገዋል። የዚያ ባህር ሰምም ተቀይሮ አረማያ በመባል ፋንታ
ዓለም ማያ ተብሎ ተሰይሟል።

፪ኛው፦ ንጉሡ ትምህርታቸውን የተማሩት በሚሽን
ትምህርት ቤት ስለነበረ በዘመኑ የነበሩት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እምነታቸው ካቶሊክ እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ አማኝ አይደሉም በሚል ጥርጣሬ ሰልጣን ለይ መውጣት የለባቸውም በሚል አስተያየት ቀርቦባቸው ነበር። ይህንን ተቃውሞ ለመከላከልና የተዋህዶ አማኝ መሆናቸውን ለማሳወቅ አማካሪዎቻቸው ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ የእስክንድርያን መንበር የያዘና በዚያም የመጀመሪያው የእስክንድርያ ፓትርያርክ(አለቃ) ስለነበርና የዚህ መንበር ተጠቃሚም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስለሆነች የቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በቤተ መንግስታቸው እንዲተክሉ ሰለመከሯቸው የመንግሰታቸውም መቀመጫ የገነተ ልዑል ቤተ መንግስት እየተባለ ይጠራ ሰለነበረ ቤተ ክርስቲያኑም መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ተብሎ ተሰይሟል።

ከመቶ አመት በላ፦ እድሜ ያስቆጠረ የቅዱስ ማርቆስ እና የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን    በመንፈሳዊ አገልግሎት  ዙርያ በጣም  በተጠናከረ  መልኩ የተለየ  አገልግሎት የሚሰጥ ደብር ነው።   ሆኖም በመግቢያው  ብሩ ምክንያት ብዙ ተግዳሮቶች   በአገልግሎቱ ላይ የገጠመው ሲሆን    ። ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና ለአገልግሎት ምቹ ለማድረግ የተዘጋጀ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ መርሐ ግብር።

ቀን ነሐሴ 30 እና ጳጉሜ 1  2017 ዓ ም
ሴፕቴምበር 5 እና 6 20 25

ከቀኑ 12:00 ጀምሮ እንደ ኢትዮጵያውያን ሰአት አቆጣጠር

Recent Causes

Please, help us to help others

    Ways you can support us

  1. You can simply use the Donate to 6kilokidusMarkos button above and we will apply the funds to any of the causes as we see fit.
  2. Alternatively, you can select a cause that appeals to you more, and give as generously as you can. And, don't forget to inform others, too.
  3. Finally, to go the extra-mile, you can Start a new cause to fundraise from your friends and family.

Whatever you choose, thank you!

Image