- Started on: 02 jun 2025
- Closing Date: 31 dec 2025
Help us build not just a centre—but a legacy of compassion and care.
የሚረዱንን እንርዳ! መስጠት መታደል ነው።
ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል በ ሊቀ ኅሩያን መለሰ አየለ እደ ኢትዮጵያን አቆጣጠር በ1998 አ/ም ተቋቋመ።
ከኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እውቅና አግኝቶ በ አዕምሮ ሕመምና በተለያዩ ደዌ ታመው በሚሰቃዮ ሕሙማን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ የሚገኝ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን አላማው ምንም አይነት ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው የአዕምሮ ሕሙማን ምግብ፣ መጠለያ፣ እዲሁም አስፈላጊውን ሕክምና እዲያገኙ በማድረግ የተሙዋላ ቤተሰባዊ ፍቅርና እንክብካቤ መስጠት ነው።
ማዕከሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ1500 በላይ የአዕምሮ ህሙማንና በተለያዩ ደዌ ታመው የሚሰቃዩ ከጎዳና እና ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት በር ላይ በማንሳት በተከራየው የሕሙማኑ ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ አስፈላጊውን መሰረታዊ ፍላጎታቸውን በሟሟላት ላይ ይገኛል።
ለ አእምሮ ህሙማኑ የሚሆን ከመንግስት ለማዕከሉ ግንባታ 3000 ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ ግንባታውን የጀመረ ሲሆን ግንባታውን ለማጠናቀቅ ያንተን፣ ያቺን፣ የኔን የኛን እርዳታ ይሻሉ።
ማዕከሉ በክራይ ሕሙማኑን የሚያስጠልልበት ቦታ አመቺ ያልሆነ በተለይም በ አሁኑ ሰአት በጣም አስጊ ሁኔታላይ ይገኛሉ።
ወድማችን ሊቀ ህሩያን ዲ/ን መለሰ ለዚ በረከት ክብር ከታደለ እኛም እያደረገ ያለውን መልካም ምግባር ልናግዘው ቀን የጣላቸው ወገኖቻችንን ነገ እነሱ የኛን የ ዲ/ን መለሰን እድል እዲያገኙ አለናችው በማለት የሚረዱንን እንርዳ ብለን እኛ በ ዪኬ የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያን ኤርትራዊያን እዲሁም ለበጎ ምግባር እጃችን የዘረጋን ሁሉ አለናቹ በማለት ቆመናል። እናተም የተቻላችውን እድታግዙን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
የሚሰጡ እጆች ብፁሀን ናቸው! መስጠት መታደል ነው።
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech