የአርሴማዊትን የኩላሊት ንቅለ-ተከላ ህክምና እናግዝ/ Arsemawit's Kidney Transplant

cause-image
  • Started by: Damtew Gebregziabher
  • For: The Organiser (Personal)
  • Started on: 22 jun 2022
  • Closing Date: 21 sep 2022

ወ/ት አርሴማዊት አባይነህ የምትባል ኢትዮጵያዊት የበቆጂ ከተማ ተወላጅ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በትውልድ ከተማዋ የተከታተች ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪዋን በአካውንቲንግ የትምህርት መስክ ተመርቃ ከሁለት ላልበለጡ ዓመታት በሁለት የግል ድርጅቶ ስታገለግል ቆይታለች።

እህታችን አርሴማዊት (የሥልክ ቁጥር +251-906-303830) በወጣትነት ዕድሜዋ ባጋጠማት የኩላሊት ሕመም ምክንያት ሐኪም በአስቸኳይ የኩላሊት ንቅለ-ተከላ ማድረግ እንዳለባት ውሳኔ በመተላለፉ የጥቁር አንበሳ ሕክምና ቦርድም የኩላሊት ንቅለ ተከላ አገልግሎት በኢትዮጵያ ስለማይሰጥ ወደ ውጪ ሀገር ሄዳ እንድትታከም ፈቃድ የሰጣት ሲሆን በአሁን ሰዓት በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት/ ደም እጥበት (Dialysis) እያደረገች ትገኛለች።

ይሁንና ለህክምናው የተጠየቀውን 30,000.00$ (ሰላሳ ሺህ የአሜሪካ ዶላር) በራሷም ሆነ በቤተሰቧ አቅም ለመሸፈን መቸገሯን በመግለጿ የወገንን ድጋፍ ማሰበሳብ የሁላችን የወገኖቿ ግዴታ ሆኗል።

የሥጦታ ትንሽ የለውምና ሁላችን እንተባበራት!

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

(From 4 donations)

ETB 10,835 of ETB 250,000 4%