- Started on: 27 nov 2025
- Closing Date: 30 apr 2027
ዋልድባ ዳልሻሕ ኪዳነ ምሕረት ገዳም የታነጸችው በ485 ዓ.ም እንደሆነ ይነገራል። ቦታውን ያቀኑት አቡነ ገብረ መስቀል ናቸው። ይህ ገዳም ከጥንት ጀምሮ የአንድነት ገዳም ነው። በዚህ ገዳም የላመና የጣመ መብል አይቀመስበትም የሞቀና የደመቀ ልብስ አይለበስበትም። ገዳሙ በብዙ ግሑሳንና ሥውራን አባቶች ተጋድሎ የከበረ ገዳም እና እጅግ ውብ የሆኑ ሥርዓተ አበው የሚከናወንበት የተለየ ቀደምት ገዳማት ነው፡፡
ይሁን እንጂ መነኰሳቱ፡ የቦታውን ታሪክና ክብር አስጠብቀው ለመቀጠል፡ ከፍተኛ ቁርጠኝነት ቢኖራቸውም ታሪኩን እና ሰርዓቱን አሰጠብቆ ለማሰቀጠል ከፍተኛ የተፈጥሮ አድጋ በመጋረጡ ምክንያት የገዳሙ አባቶች የልማት ኮሚቴ አቋቁመው ገዳሙ እራሱን በመቻል ከተረጂነት መንፈስ ወጥቶ በገዳሙ ውስጥ ያሉ ከ 500 በላይ መነኰሳትን አረጋውያን ዓቅመ ደካሞችን ከመርዳትም አልፎ የአብነት ትምህርት ቤቱን በማስፋፋት የልህቅት ማአክል ማድረግ ጽኑ ፍላጎቱ ነው።
ለዋልድባ እንዳልሽህ ኪዳነምህረት ገዳም ርዳት በቀጥታ ስርጭት እየተሰበሰበ ይገኛል። እናንተም የበረክቱ ተካፍይ እንድትሆኑ ከሀገር ቤተም ከውጭም በወገንፈንድ ተሳተፉ።
Copyright 2026 - Wegenfund | Powered by WegenTech