United Amhara

cause-image
  • Started by: Mengistu Ayele
  • For: UACDA-Logo
  • Started on: 30 dec 2021
  • Closing Date: 30 dec 2022

የተባበሩት አማራ በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበር በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝና ዘላቂ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚከተሉትን ፕሮጅክቶች ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከፊል ወላጅ አልባ እና ወላጅ አልባ ህፃናት በአማራ እና አፋር ክልሎች ጦርነት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የእንክብካቤ እና የድጋፍ ማድረግ ፤ በአማራ እና አፋር ክልል በጦርነት የተፈናቀሉ እናቶችና ጨቅላ ህጻናት መታደግ ፤ ከአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን የስነ ልቦና ድጋፍ ማድረግ ፤ በአማራ ክልል በተደረገው የኢኮኖሚ ድጋፍ የፋኖ እና ‘ሚኒሻ’ ቤተሰቦችን ማጠናከር ፤ በአማራ እና አፋር ክልል ጦርነት ለተጎዱ ሴቶች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ፡፡

ከጦርነቱ በፊትም UNDP በ2016 ባስጠናው ጥናት መሰረት ከሶማሊና አፋር ክልል ቀጥሎ የአማራ ክልል በ47.65% ከፍተኛ የማይምነት (illiteracy) ቁጥር እንዳለ ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም በትልልቅና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ስርጭት የአማራ ክልል ዝቅተኛ ድርሻ እንደነበረው በግልጽ አሳይቷል (UNDP, 2016).1 ይህንን ለመቀየር የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን የተገኘው ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጓል፡፡

የአማራ ህዝብ በተለይ ላለፉት 27 ዓመታት በሀገሪቱ ውስጥ ከመጣው የኢኮኖሚ እድገት ተጠቃሚ እንዳልነበር የአለም ባንክ ባደረገው ጥናት ጭምር አረጋግጧል፡፡ ይህን የአለም ባንክ የጥናት ውጤት ብዙ የአገር ውስጥ አጥኝዎችም አረጋግጠዋል፡፡ በክልሉ በቂ የሆነ የመንገድ፤ የጤና፤ የመብራትና የትምህረት አገልግሎት እንደሌለ ጥናቱ አመልክቷል፡፡ በክልሉ ከ900 በላይ የዳስ ትምህርት ቤቶች እንዳሉና በቂና ጥራት ያለው የትምህርት ግባት የሌላቸው መሆናቸውን መንግስትም አመልክቷል፡፡ የትምህርት መስኩን በተመለከተ ባጠቃላይ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ ትምህርት ቤቶች 16% ብቻ ሲሆኑ 84% የሚሆኑት መስፈርቱን የማያሟሉ መሆኑን የመንግስት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

አሁን የተከሰተው ጦርነት ከላይ የተገለጹትን ችግሮች በጣም ያባባሳቸው በመሆኑ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የእራዳት እጃቸውን በመዘርጋት እንዲተባባሩ እና በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳውን ሕዝብ መልሶ ለማቋቋም እንዲተጉ እንጠይቃለን።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 5,013 of ETB 1,000,000 1%