የ፴፻ ዓመቱ ጣና ቂርቆስና የነገ ልዕልናው

cause-image
  • Started by: Tana Kirkos Gedam
  • For: EOTC_logo
  • Started on: 04 sep 2026
  • Closing Date: 31 dec 2027

በኢትዮጰ‍እያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ስር የሚገኘው ጥንታዊ ና ታሪካዊ የሆነው የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የታቦተ ጽዮን ማረፊያ ፤የድንግል ማርያም የቃል ኪዳኗ ደሴት ፤ የቅዱስ ያሬድ ና የአቡነ ሰላማ መካነ ምሥጢር የሆነና ከ፱፻፹፪ ዓመተ ዓለም ጀምሮ አምልኮተ እግዚአብሔርን ከድንቅ ታሪክ ና ከከበሩ ቅርሶች ጋር ጠብ'ቆ ያቆየ ገዳም እንደሆነ ገዳሙ ራሱ ሕያው ምስክር ነው።

ገዳማችን የገዳሙን የሦስት ሺ ዓመት የአምልኮተ እግዚአብሔር ጉዞ ለማሳወቅ ፤ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ግንባታ ያደረገውን አስተዋጽኦ ለመግለጥ ፤ ገዳሙን በእውቀት ፣ በመንፈሳዊ ሕይወትና በልማት አጠናክሮ በልዕልናው እንዲቀጥል ለማድረግ አቅዶ ተነስቷል።

ገዳሙ በአሁኑ ሰዓት ከ350 በላይ መነኮሳት እና ከ200 በላይ ደቀመዛሙርት በውስጡ የሚኖሩበት ሲሆን ከአሁን በፊት ገዳሙ ይተዳደርበት የነበረው የ እርሻ መሬት በእንቦጭ አረም ምክንያት በመጥፋቱ በአሁኑ ሰዓት የሚተዳደርበት ምንም ቋሚ ገቢ የሌለው በመሆኑ ምክንያት ታላቅ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበት ይገኛል። በመሆኑም ይህን የተጋረጠበትን የሕልውና አደጋ ተሻግሮ ወደ ቀደመ የክብሩ ልዕልና ይመለስ ዘንድ “ የ፴፻ ዓመቱ ጣና ቂርቆስና የነገ ልዕልናው” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ጳጉሜን 2፣3፣4 / 2018 ዓ.ም የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር ለማድረግ ተዘጋጅቷል።

ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 2,140,872 of ETB 50,000,000 4%