ኑ! እጅ ለእጅ ተያይዘን የራሳችንን ችግር በራሳችን እንፍታ

cause-image
  • Started by: Paegume Amst
  • For: logo
  • Started on: 21 apr 2024
  • Closing Date: 21 dec 2027

“ኑ! እጅ ለእጅ ተያይዘን የራሳችንን ችግር በራሳችን እንፍታ”

ጳጉሜን አምስት በጎ አድራጎት ድርጅት በ 2011 ዓ/ም የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በተሰጠው ስልጣን በመዝገብ ቁጥር 4434 ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡
የድርጅቱ ዋና ዓላማ መስራት የሚችል ጉልበት፤ መማር የሚችል አእምሮ ይዘው በተለያዩ ምክንያት ወደጎዳና በመውጣት ለተለያዩ አደንዛዥ ዕፅ፤ ሱስ እና ለተስፋ መቁረጥ ተጋልጠው ለአገርም ሆነ ለህብረተሰቡ ትልቅ ተግዳሮት የሆኑትን ዜጎች ከጎዳና ላይ በማንሳት እራሳቸውን እስኪችሉ አስፈላጊ የሚባለውን ስልጠና፤ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ከተረጂነት እራሳቸውን በማስቻል ወደረጂነት ማሸጋገር ነው።
ድርጅቱም በዋናነት ጎዳና ላይ ያሉ ችግረኛ እና ምስኪን ወገኖቻችንን ከጎዳና ላይ በማንሳት
ቤት በመከራየት
• የስነልቦና ስልጠና መስጠት
• ወርሃዊ አስቤዛቸውን መሸፈን
• የአልባሳት ና የቁሳቁስ ድጋፍ ማቅረብ
• የስራ እድል ማመቻቸት
• ትምህርት እንዲማሩ ማድረግ
• ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ እና ባሉበት እንዲሰሩ ማድረግ
• የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማመቻቸት ወዘተ ዘላቂ መፍትሄ ላይ በማተኮር እየሰራ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ ፍቃድ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ላለፉት አምስት(5) አመታት ጎዳና ላይ ላሉ ከ 10,000 ሺህ በላይ ችግረኛ እና ምስኪን ወገኖቻችንን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ ሊያደርግ ችሏል፡፡
ድርጅቱ አሁንም ይህንኑ ስራውን ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠል ጎዳና ላይ ላሉ ለሰላሳ (30) ወጣት ወገኖቻችንን ከጎዳና ላይ በማንሳት ከሚመለከተው አካላት ጋር ጥምረት በመፍጠት እየሰራ ይገኛል፡፡ እናንተም ይህን በጎ አላማ በመረዳት እነዚህን እቅዶች ለማሳካት የእርስዎ ድጋፍ እና ትብብር ከወዲሁ አስፈላጊ በመሆኑ “የራሳችንን ችግር በራሳችን እንፍታ” በሚል መሪ ቃል ከጎናችን ሆነው ወገኖቻችንን ከጎዳና ላይ ለማንሳት በባለቤትነት ተሳታፊ በመሆን የተቋሙን ህዝባዊነት በማረጋገጥ፦ የህሊና እርካታ እንዲያገኙ ስንጋብዝዎት በታላቅ አክብሮት ነው።
----------------------------------------------------------------------
ለፕሮጀክቱ ሚያስፈልገው ብር 2,000,000 ብር // 35,714.28 ዶላር
ለበለጠ መረጃ 09-11-67-12-39//09-35-02-66-63
ኢ-ሜል፡-peagumeamst88@gmail.com
https://pagumenamstcharity.org/

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 210 of ETB 2,000,000 0%