ወደ አዲሱ ምዕራፍ አብረን እንሻገር - ማኅበረ ቅዱሳን

cause-image
  • Started by: Mahbere Kidusan
  • For: logo.jpg
  • Started on: 28 aug 2026
  • Closing Date: 31 dec 2026

ማኅበረ ቅዱሳን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና አገልገሎት መስጠት ከጀመረበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ 34 ዓመት ሆኖታል።በዚህ ረዥም በሚባል የአገልግሎት ዘመን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመጸም ውጤታማ ሥራዎችን ሰርቷል፡፡በተለይም ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ የቅዱስ ወንጌልና የመረጃ ተቀዳሚ የቤተ ክርስቲያን ድምጽ በመሆን ዓመታትን አስቆጥሯል።

በመሆኑም ከማኅበሩ አሁን ላይ ቤተ ክርስቲያኗ በሚዲያው ዘርፍ የምጠብቅበትን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለመፈጸምና ለማስፈጸም በየዘመኑ አስፈላጊ ለውጦችና ስትራቴጂዎችን መቀየስና አዳዲስ
ስልቶችን መከተል የሚጠበቅ ተግባር ስለሆነ ቤተ ክርስቲያንን የሚመጥን ደረጃው ከፍ ያለ ሁለገብ አገልግሎት ለመፈጸም የሚያስችል ዘመናዊ ስቱዲዮ በመገንባት፣የሚዲያ ቁሳቁሶችንና ባለሙያዎችን ለማሟላትና በ7 ቋንቋ የሚሰጠውን የቴሌዥን እና የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት ለማሳደግ ከፍተኛ የሆነ ሀብት የሚጠይቅ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ዓለም ወደ ዲጂታል ዘመን በፍጥነት እየተሸጋገረች ነው።የመረጃ ፍሰት፣ የዕውቀት ሥርጭት፣ የትምህርት አቅርቦትና የማኅበራዊ ተፅዕኖ ከባህላዊ የሚዲያ መድረኮች በመውጣት ወደ ዲጂታል ፕላትፎርሞች እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።

በዚህ የለውጥ ዘመን የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልዕኮ፣ የእምነት ትምህርት፣ የሥነ-ምግባር እሴቶችና የትውልድ ግንባታ ተልዕኮ በዘመኑ የመገናኛ መንገዶች ለማድረስ የሚዲያ አቅሙን ማጠናከር የሚጠይቅ ወሳኝ ወቅት ላይ ይገኛል። ይህንን ተግባር ለመደገፍ ከጳጉሜን 1 ቀን ጀምሮ እስከ 5 ድረስ “ወደ አዲሱ ምዕራፍ አብረን እንሻገር” በሚል መሪ ቃል ከማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ በተጨማሪ በታወቂ ዩቲዩቨሮችና ቲክቶከሮች የሚተላለፍ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮችን ያካተተ የሃብት ማሰባሰቢያ የቃልኪዳን መድረክ ይከናወናል። በዚህ የበረከት ሥራ እንድትሳተፉ ጥርያችን ይድረሳችሁ።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 1,100 of ETB 59,000,000 0%