ለመፅደቅ

cause-image
  • Started by: Eshetu Mitiku
  • For: Logo lemetsdek
  • Started on: 15 oct 2025
  • Closing Date: 31 aug 2026

ከኮሜድያን እሸቱ መለሰ (ዶንኪ ቲዩብ) የቀረበ የህይወት አድን ጥሪ

እኔ ኮሜድያን እሸቱ መለሰ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በእግዚአብሔር ፍጹም ቸርነት እና በታማኝ ተከታዮቻችን ድጋፍ፣ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀዳሚ የሆነውን ዶንኪ ቲዩብ የዩቲዩብ ቻናል ገንብቻለሁ።
ከ 3,100,000 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ) በላይ ታማኝ ተከታዮችን አፍርተናል።

በቅዱስ እግዚአብሔር ፍጹም ቸርነት ከ1.2 ቢሊዮን ብር (አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር) በላይ ለበጎ አድራጎት ገንዘብ ማሰባሰብ ችለናል።

ዋና ዋና በጎ አድራጎት ተግባራት (የተሰበሰበው ድጋፍ):-
- ለታማሚ ልጅ ላላቸው እናቶች (ከ380 በላይ እናቶች) ፡ ከ100,000,000 ብር በላይ
- ለመቄዶንያ የአእምሮ ህሙማን እና አረጋውያን መርጃ ፡ 250,000,000 ብር
- ለአሜሪካው የቅዱስ ዮሐንስ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም ፡ 350,000,000 ብር
- ለኳታር ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ፡ 130,000,000 ብር
- ለለንደን ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፡ 221,000,000 ብር

ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ሥራዎች ትምህርት የወሰድኩት እኔ መስራቹ፣ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ፣ ቀሪ ዘመኔን አቅጣጫ ለመቀየር ወስኛለሁ። ከአሁን በኋላ ትኩረቴን ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ በመዝመት፡- ታማሚ ልጅ ያላቸውን እናቶች በማገልገል እና ቀሪ ሕይወታቸውን የሚያስተካክል ዘላቂ ሥራ በመስጠት ላይ አደርጋለሁ። ይህንኑ ስራ ለመጀመር እግዚያብሄር ፈቅዶ በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ የገጠር አካባቢ ላይ መስከረም 26/2018 ዓ.ም. በይፋ የተረከብነው 60,000 ካሬ ሜትር መሬት አለ ፡፡ ይህ መሬት በምንረከብበት ወቅት አካባቢውም እጅግ የሚያሳዝን የገጠር ማህበረሰብ የሚኖርበት ሲሆን፣ ሕዝቡ ለዘመናት በሦስት ዋና ዋና ችግሮች ምክንያት በእጅጉ ተጎድቷል፡
1. የውሃ እጦት
2. የመንገድ እጦት
3. የመብራት አገልግሎት እጦት

የውሃ፣ የመንገድ እና የመብራት አገልግሎት ባለማግኘታቸው ምክንያት የማኅበረሰቡ ሕይወት እያለፈ ሲሆን፣ ይህንን ዘላቂ ችግር ለመፍታት የሚያስችል ሥራ ለመሥራት ለማህበረሰቡ ቃል ገብተናል።

ውድ ወገኖቼ፣ ዶንኪ ቲዩብ እስካሁን ድረስ በብርታቱ ያከናወነው ሁሉ የእናንተ የአጋርነት ውጤት ነው። አሁን ደግሞ የዚህ ትልቅ የሕይወት አድን ፕሮጀክት አካል እንድትሆኑ በትህትና ጥሪያችንን እናቀርባለን። የመጀመሪያው እና ቀዳሚው የሕይወት አድን ተግባር:
የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ: የተጠሙ የአካባቢው ነዋሪዎችን አብረን በማጠጣት ከዘመናት ችግር እናውጣቸው።

"እነዚህን የተጠሙ ወገኖቻችንን ውሃ አጠጥተን፣ መንገዱን አሰርተን ፤ አብረን እንጽደቅ!"

ለዚህ ዘላቂ የልማት ስራ የሚሆን

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 54,634 of ETB 40,000,000 0%