- Started on: 22 jun 2026
- Closing Date: 31 aug 2026
ቁልቢ ገብርኤል አርሲ ገብርኤልን ሊገነባ ነዉ፡፡
ታላቁ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመቱን ሙሉ ሕዝበ ክርስቲያን የማይለየው በተለይም የታህሣስ እና ሐምሌ ዓመታዊ በዓላት ደግሞ እጅግ በርካታ ስዕለቱ የሞላለትና እንዲሁ ለተራዳኢነቱ ፍቅሩን ለመግለጥ በሚመጣ ህዝብ የሚጥለቀለቅ ገዳም ነው ።
እንደየአቅማችንም የምንለግሰው ስዕለት አስራት በኩራት ምፅዋትና ሌሎች ስጦታዎቻችን በሙሉ ከ50 ዓመታት በፊት ጀምሮ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት እንዲተላለፍ ተወስኖ በሚገኘው ጠቅላላ ገቢ …
በሁሉም አህጉረ ስብከት ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት፣ የአብነት ት/ቤቶች፣መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ፣አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኮሌጅ፣ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ እና ለሌሎችም የትምህርት ተቋማት መመስረትና ለበርካታ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና ቋሚ መሰረተ ልማቶች እንዲውል በመደረጉ ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ችግር ፈቺ፣ የልማት ተሳታፊ፣ ድርና ማግ፣ ምሰሦና ማገር ለመሆን በቅቷል።
በእነኚህ ረጅም ዓመታት ለቁልቢ በሰጣችሁት ስጦታ በየአቅራቢያሁ ያሉ የቤተክርስቲያን መሰረተ ልማቶች ሁሉ የቁልቢ ገብርኤል አሻራ ታትሞባቸዋል ።
በእድሳት ላይ የሚገኘው ቁልቢ ገብርኤል በቅርቡ በተለመደው ቤተክርስትያንን የማቅናት ተግባሩ የመቃጠል አደጋ የደረሰበት የአርሲ ጠለታ ገብርኤልን ለማስገንባት በዝግጅት ላይ ይገኛል ።
የቁልቢ ውለታ ያለባችሁ ተቋማት፣ ስዕለታችሁ የተሰማ ፣ በተስፋ የምትጠብቁ ምዕመናን ኑ የዕንባ አባሹ ቁልቢ ገብርኤልን እናድስ የአርሲን ጠለታ እንገንባ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።
Copyright 2026 - Wegenfund | Powered by WegenTech