በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ ወደ ቀደመ ክብሩ እንመልሰው

cause-image
  • Started by: Aba leykun Wondifraw
  • For: eotc-logo-original-2
  • Started on: 03 jul 2025
  • Closing Date: 30 sep 2025

ጥንታዊውና የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ በመባል የሚታወቀው ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም፣ የዕውቀትና የጥበብ ማእከል፣ የሊቃውንት መፍለቂያ፣ የድርሰትና የትርጓሜ ከፍተኛ ጉባኤ ቤት፣ የአሠረ ምንኵስና አስኬማ መላእክት መገኛ ነው፡፡ ቅዱስ አቡነ ሰላማ የባረኩት፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳሙን የመሠረቱትና ያሳደጉት፣ አቡነ ተክለሃይማኖት የመነኰሱበት፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተማሩበት፣ የእነ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፣ የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ የአቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የአቡነ ሠረቀ ብርሃን፣ የአቡነ በግዑ፣ የአቡነ ብስጣውሮስ እና አእላፍ ጻድቃን በረከትና ቃልኪዳን መካነ ጽድቅ፣ የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የቅኔና የሥነ ጽሑፍ፣ የትርጓሜ፣ የሥነ ጥበብ፣ የዜማና የቅዳሴ ሁለንተናዊ የዕውቀት ምሰሶ፣ መዝገበ አእምሮ፣ መካነ ቅርስ፣ ባህረ ጥበብ፣ ፍኖተ አሚንና የእምነት ምስክር ነው።

ያለማቋረጥ ከ1400 ዓመታት በላይ ተጠብቆ የቆየውን ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ ለመላው ዓለም ማስተዋወቅ ስለሚገባ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመልስ ከሰኔ 27 እስከ 29 እዚያው ከገዳሙ በቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ ይደረጋል። በኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም ያአላችሁ ክርስቲያኖች ለዚህ በጎ ዓላማ እንድትሳትፉ ጥሪ ቀረቦላችኋል።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 132,130 of ETB 50,000,000 0%