ቤተክርስቲያን አብረን እንስራ

cause-image
  • Started by: Melake Salem Qesis Solomon Sahlemariam
  • For: eotc-logo-original-2
  • Started on: 17 nov 2025
  • Closing Date: 31 jul 2026

የሐዋሳ ደብረ ሳሌም ቅዱስ ቂርቆስ ወቅዱስ ሚናስ ቤተክርስቲያን በሲዳማ ሀገረ ስብከት ብርቱ ጥረት በቅርብ ከተተከሉ ዐቢያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ሲሆን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለመፈጸም የሚያስችል ዐውደ ምሕረት የሌለው፤ ከፊት ከጀርባ ከግራ ከቀኝ በሁሉም አቅጣጫ የተጣበበና ቤተልሔሙና ቤተክርስቲያኑ መሐል ክፍተት ባለመኖሩ የተጋጠመ ነው:: ከዚህም የተነሣ በበዓለ ንግሥ ታቦታቱ ዑደት ለማድረግ እንኳን ይቸገራሉ::

እንኳን ቤተክርስቲያን የአንድ ግለሰብ ቤት እንኳን አጥር ይኖረዋል:: ከአጥር አቅም እንኳን አጥር የሌላትን ይህችን ቤተክርስቲያን መደገፍ ይገባል:: ቤተክርስቲያን ከፍ ብላ ልትታይ ይገባታል:: በቤቶች መሐል ያለችውን ቤተክርስቲያን ከፍ አድርገን እንሥራ:: ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋትን ልጆቿ ያውቃሉ::

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 100 of ETB 20,000,000 0%