ኑ የገላን ጉራ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን እንሥራ

cause-image
  • Started by: Gelan Gura St Urael Church
  • For: EOTC_logo
  • Started on: 18 nov 2026
  • Closing Date: 16 feb 2027

ከታላቁ ደብር ከካዛንቺስ ቅዱስ ዑራኤል ከመንበረ መንግስት ግቢ ገብርኤል እና ከተለያዩ አካባቢዎች በልማት ተነስተው ወደ ገላን ጉራ ለገቡ ህዝበ ክርስቲያን ከመንግስት በተሰጠ 2000 ካሬ ቦታ ላይ የመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶ ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ከጀመር 3 (ሶስት) ወር አልፎታል።አሁንም በምዕመናኑ ጥያቄ መሰረት የገናናው መልአከ የመጋቤ ሐዲስ ቅዱስ ገብርኤልን ፅላት ጥቅምት 21 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ወደ ደብሩ ገብቷል።

ሆኖም መቃኞ ቤተክርስቲያኑ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በመሆኑ ቅዝቃዜው በዕድሜ ለገፉ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ለህመም እየተጋለጡብን በመሆኑ እና ካለው የምዕመናን ብዛት አንፃር አነስተኛ እና ሀይማኖታዊ ስርአትን ለመፈፀም እንዲሁም ለአገልግሎት አስቸጋሪ ስለሆነብን እና የቤተልሔም ፡የግብር ቤት ፡የክርስትና ቤት፡የግቢውአጥር፡ የካህናት ማረፊያ፡እና ሌሎች ለአገልግሎት የሚያስፈልጉ የጽ/ቤት ቢሮዎች እንዲሁም መሰረታዊ የቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት ለማሟላት ይቻል ዘንድ በመላው ዓለም ያላችሁ የመልአኩ ዑራኤል እና የቅዱስ ገብርኤል ወዳጅ ሁሉ የተቻለውን በማድርግ የዚህን ከታላላቅ አድባራት የመጡ ህዝበ ክርስቲያን መፅናኛ የእግዚአብሔርን ቤት እንድንደግፍ እያልን ጥሪ እናስተላልፋለን።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 0 of ETB 10,000,000 0%