በሻሸመኔ እና አካባቢው የተጎዱ ካህናትና ምዕመናን እንደግፍ

cause-image
  • Started on: 22 feb 2023
  • Closing Date: 23 may 2023

በመንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የነበሩ አንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በተከሰተው በወቅታዊ ችግር ምክንያት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቁ በነበሩ ካህናትና ምዕመናን ላይ የተለያየ አይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት ደርሷል፡፡ በዚህም ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ፣ ልዩ ልዩ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ እንዲሁም በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በቀጣይ ተንቀሳቀስው ስራ በመስራት ገቢ ማገኝት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ያሉ በርካታ ምዕመናን እና ካህናት እንደሚገኙ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በመሆኑም እነዚህን ምዕመናን እና ካህናት በመደገፍ የህክምና፣ የማፅናኛ እና የማቋቋሚያ ድጋፍ ማድረግ ሀይማኖታዊ እና ሞራላዊ ግዴታ በመሆኑ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ መልካም ፍቃድ እና መመሪያ ሰጪነት ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ ስለሆነም በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች የሰማዕታቱን ቤተሰቦችና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ለመደገፍ እጃችሁን እድትዘረጉ ከሰማዕታቱ በረከት እንድትሳተፉ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በዘመናችን በዓይናችን ያየናቸውን ሰማዕታት እናክብር

Due to recent events, members of The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church who were at church for worship, and those who were at church to protect their parishes sacrificed their precious lives, were seriously injured or are receiving treatment at hospitals following the attacks on EOTC churches and its followers.

This Cause is to support the families of those who were martyred, and all others seriously affected by this. Your generous donation will go directly to the victims and their families in the Dioceses of Sidama Region, West Arsi & Gedio Zones, and Amaro & Burji Special Weredas.

We have seen martyrs in this day and age -- let us honour them!

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 10,526 of ETB 160,000,000 0%