ኑ የበቆጂ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንጨርስ

cause-image
  • Started by: Amare Zemariam
  • For: EOTC_logo
  • Started on: 21 feb 2024
  • Closing Date: 31 may 2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ ልቡ እንዳሰበ ይስጥ። 2ኛ ቆሮ 9:7

በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአርሲ ሀገረ ስብከት በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ የበቆጂ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቸርነት በእናንተ በልጆቿ ትጋትና ለጋስነት ህንጻ ቤተክርስቲያኗ ከዚህ ከሚታየው ደረጃ ደርሷል። እነሆ አሁን የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። በቆጂን እንኳን ያመረተችውን የበላ ውሃዋን የጠጣ ቀርቶ ዓለም ያውቃታል ይናፍቃታል።

ለዚች ባለውለታ ከተማ እና ህዝበ ክርስቲያን በዚህ የበረከት ጥሪ በመሳተፍ አክብሮታችንን እንግለጽ።
እኛ የሱን ቤት ለመስራት ስንነሳ እርሱ ደግሞ የኛን ቤት በሶስት እጥፍ ሊሳራ የተመነ ነው።
ኑ ከያላችሁበት የበረከቱ ተሳታፊ ሁኑ። እጅግ ደስ የሚያሰኘውን ሥራ ለመስራት እንፍጠን።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 25,031 of ETB 1,000,000 3%