"በኃይል ሰላም በጌጠኛው ቤትህ ልማት ይሁን" መዝ 121፥7

cause-image
  • Started by: ማህበረ 30
  • For: 1000018621.jpg
  • Started on: 09 mar 2026
  • Closing Date: 14 jul 2026

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት በጉባ ላፍቶ የሚገኘውን የዲጎ ደብረ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሆነውን የአዳሪ ትምህርት ቤትን እንታደግ!
"ትላልቅ አብያተ ክርስያናት ገንብተን ትልልቅ ሊቃውንትን ከምናጣ ትልልቅ ሊቃውንትን አፍርተን እንደጥንቱ በድንኳን ብንገለገል ይሻለናል።" ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ
ይህ የቅድስት ቤተክርስቲያን የጀርባ አጥንት የሊቃውንት መፍለቂያ የጠቢባን ትምህርት ቤት የሆነው የአብነት ትምህርት ቤት በሰሜኑ ክፍል ባለው የሰላም እጦትና በተለያዩ ምክንያቶች አዳሪ ጉባኤ ቤቱ በጣም እየተፈተነ ይገኛል።
ይህንን የአዳሪ ትምህርት ቤቱን ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና ራሱን እንዲችል ለማድረግ፣ ያጭር ጊዜ እቅዳችንን ለማሳካት ዘመናዊ የልብስ ማሽኖችን፣ ዘመናዊ የሽመና ማሽን በመግዛት ጉባኤ ቤቱን ለማጠናከር ትተባበሩን ዘንድ በሊቃውንቱ አምላክ ስም እንማጽናለን

ሙሉ ገቢው ለአብነት ት/ቤት ዘላቂ ፕሮጀክት ማስፈጸሚ የሚውል።
ለበለጠ መረጃ 0975350256/0912048588/ 0926764646

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 2,000 of ETB 955,000 0%