Basic Computer training for Visually Impaired women

cause-image
  • Started by: Yosef Adane
  • For: Salu logo.png
  • Started on: 03 feb 2023
  • Closing Date: 03 feb 2024

ላለፉት26 ዓመታት ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ነገር ግን ሰርተው መለወጥ የሚችሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አካል ጉዳተኞችና ተጠቂ የማሕበረሰብ ክፍሎችን በተለያዩ የዕደጥበብ ምርቶች አሰልጥኖ በሥራ ላይ ሲያሰማራ የቆየው ማህበራችን ሳሉ መረዳዳት የዓይነስውራንና አካል ጉዳተኞች ማህበር በኮቪድ 19 አለማቀፍ ወረረሽኝና ከዚያም ቀጥሎ በሰሜኑ የአገራችን ከፍል በተከሰተው አለመረጋጋትና የርስ-በርስ ግጭት ምክንያት ቀደም ሲል ድጋፍ ሲያደርጉለት የነበሩ አለማቀፍ ለጋሾች ድጋፋቸውን በማቋረጣቸው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ ይገኛል፡፡
ማሕበራችን ከምሥረታው ጀምሮ ከተለያዩ ክልሎችና ክፍለ ከተሞች እንዲሁም ከእምነት ተቋማት አካባቢ ከልመና ይልቅ ሰርተው በጥረታቸው ራሳቸውን ለመለወጥ ፈቃደኛ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓይነስዉራንና አካል ጉዳተኞችን አሰባሰቦ በማሰልጠንና በሥራ በማሰማራት ስኬታማ ተግባር ያከናወነ ሲሆን አሁን ግን ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች በገጠመን የገንዘበና የቁሳቁስ እጥረት ሳቢያ በተለይም ለጥሬ ዕቃ ግዢና ለአስተዳደራዊ ወጪ የሚሆን ገንዘብ በማጣታችን ማህበሩ ሊፈርስና ሰርተው ለመለወጥ ፈቃደኛ የነበሩ አካል ጉዳተኞች ቀደም ሲል ንቀው ወደተዉት ልመና ሊመለሱብን በመሆኑ ይህ ከመሆኑ በፊት የድጋፍ ጥሪ ማሰማት ስለሚገባን ይህን የድጋፍ ጥያቄ ለወገን ማቅረብ ግድ ሆኖብናል፡፡
ስለዚህ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና የመርዳት አቅምና ፈቃደኝነት ያላቸው የዜግነት ግዴታቸዉን ለመወጣት ካሉበትም ሆነ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኘውን የሥራ ቦታችንን በመጎበኘት ልቦናችሁ በፈቀደ መጠን በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ እንድትደግፉን በታላቅ አክብሮትና ትህትና እንጠይቃለን፡፡
የባንክ ሂሳብ ቁጥራችን ዳሸን ባንክ-0010007935005 እና ኢ/ት ንግድ ባንክ 1000357433324
የስልክ ቁጥሮቻችን 251-113698933/251-912103947 ኢማል- saluethiopia@gmail.com

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 0 of ETB 2,000,000 0%