- Started on: 13 mar 2023
- Closing Date: 10 jun 2023
በሀገራችን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት እና ጦርነቱ ባስከተላቸው ቀውሶች ምክንያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ኦርቶዶክሳውያንና ሌሎች ዜጎች ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ ይታወቃል። ጦርነቱ ከባድ ጉዳት ካደረሰባቸው አካባቢዎች መሃል የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት (ሰቆጣ እና አካባቢው) አንዱ ሲሆን በዚህ አካባቢ በተካሄደው ጦርነት እና ድርቅ ምክንያት ከሰባ ሺህ በላይ ሰዎች አስከ አሁን ድረስ በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሥር ባሉ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ተጠልለው እየተረዱ ይገኛሉ።
እነዚህን ወገኖቻችንን ለመርዳት እና ወደቀያቸው ለመመለስ (መልሶ ለማቋቋም) በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ለወገናችሁ በምትችሉት ሁሉ በዚህ በወገን ፈንድ በኩል ርዳታችሁን እንድታደርሱልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech