- Started on: 25 aug 2025
- Closing Date: 30 dec 2025
የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተው በ፲፱፲፮(1916) ዓ.ም በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ነው። ቤተ ክርስቲያኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው በአዲስ አበባ ከፍተኛ ፲፩(11) ክልል ውስጥ በቀድሞው ገነተ ልዑል ቤተ መንግስት በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ በስተምዕራብ ቀድሞ እቴጌ መነን አሁን ደግሞ የካቲት ፲፪(12) በሚባለው ትምህርት ቤት በስተደቡብ ባለው ቦታ ላይ ነበር። በዚያን ጊዜ ተሰርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን አነስ ያለ ቢሆንም እጅግ በጣም ያምር እንደነበረ ወህይወተ ሥጋ ያሉ አባቶች ይናገራሉ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ቤተ ክርስቲያን ለ፲(10) ዓመታት ያህል ካገለገለ በሇላ ደጃዝማች ወንድይራድ የተባሉ አባት ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ቤተ ክርስቲያኑ አሁን ካለበት ቦታ ላይ ተዛውሮ እንዲሰራ በ፲፱፻፳፭(1925) ዓ.ም ጥያቄ ቀርቦ በንጉሡ ተጠንቶ ትክክለኛነቱ ስለታመነበት በደጃዝማቹ ገበዝነት (ኃላፊነት) በንጉሡ ገንዘብ አሁን ያለው ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ተጀመረ።በ ፲፱፻፳፮ ዓ.ም ሥራው ተጠቃሎ ጳጳሳት በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ቤተ ክርስቲያኑ አገልግሎት መሥጠት ከጀመረ ጀምሮ ለ ፬ ጊዜ ያህል እድሳት ተደርጎለታል።
ከመቶ አመት በላይ፦ እድሜ ያስቆጠረ የቅዱስ ማርቆስ እና የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በጣም በተጠናከረ መልኩ የተለየ አገልግሎት የሚሰጥ ደብር ነው። ሆኖም በመግቢያው ብሩ ምክንያት ብዙ ተግዳሮቶች በአገልግሎቱ ላይ የገጠመው ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና ለአገልግሎት ምቹ ለማድረግ የተዘጋጀ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ መርሐ ግብር
በ ነሐሴ 30 እና ጳጉሜ 1 2017 ዓ ም
(September 5 እና 6 20 25)
ከቀኑ 12:00 ጀምሮ በኢትያጵያ ሰዓት
በመላው ዓለም የምትገኙ ምዕመናን በቀጥታ በወገንፈንድ መለገስ ትችላላችሁ።
ረደኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech