የግቢ ጉባኤያትን አገልግሎት በመደገፍ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ትውልድን እናንጽ !

cause-image
  • Started by: Esubalew Geletu
  • For: logo.jpg
  • Started on: 12 apr 2024
  • Closing Date: 07 jun 2024

በግንቦት ልደታ ግቢ ጉባኤዎቻችንን እናስብ፤ አደራችንንም እንወጣ !

ማኅበረ ቅዱሳን በግቢ ጉባኤት በሚሰጠው አገልግሎት ግቢ ጉባኤያትን በመመሥረት፣ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ፣ መማሪያ መጽሐፍትን በማዘጋጀት፣ መምህራንን በመመደብ ተከታታይ መሠረታዊ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እየሰጠ በአደራ መስቀል እና በአባቶች ቡራኬ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ አገልግሎቱም ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተተኪ አገልጋዮች፣ መሪዎችንና አርአያነት ያለው ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን በማፍራት በመልካም ሥነ ምግባር የታነጸ፣ ሙስናን የሚጸየፍ፣ ሙያውን አክብሮ የሚሠራ እና ያስተማረውን ማኅበረሰብ የሚክስ ትውልድ እንዲቀጥል በማድረግ ከፍተኛ ውጤቶችን አምጥቷል፡፡

ይህንንም ለማስቀጠል፡ ለግቢ ጉባኤያት አገልግሎት መምህራን፣ ለአስተባባሪዎች፣ ለመማሪያ ቦታዎች ግንባታ፣ ለምቹ መማር ማስተማሩ ግብአት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ድጋፍ እናድርግ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡- 0904155477 ያግኙን

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 200 of ETB 2,000,000 0%