ልገሳ ለክበበፀሐይ!

cause-image
  • Started by: Lemlem Tsegay
  • For: Sele Enat Logo.jpg
  • Started on: 27 dec 2022
  • Closing Date: 27 mar 2023

ክበበ ፀሐይ ጊዚያዊ የሕፃናት ማቆያ ማዕከል በ1956 የተቋቋመ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኝ ዕድሚያቸው ከ0 እስከ 8 ዓመት የሚገኙ ወላጅ/አሳዳጊ የሌላቸው እና ለጥቃት የተጋለጡ ሕፃናት የሚያድጉበት ማሳደጊያ ነው። ክበበፀሃይ መሰረታዊ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ቢሆንም የልጆቹን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ምንም ዓይነት የህክምና ተቋም የለውም። በመሆኑም ህፃናት ብዙ ጊዜ ወደተጨናነቁ እና አስፈላጊውን ትኩረት እና እንክብካቤ ወደማይሰጡ ትልልቅ ሆስፒታሎች ይላካሉ። በዚህም ምክንያት በቀላሉ ሊተርፍ የሚችል ህይወት ያልፋል::
ይህንን ችግር የተረዳ ቢ.ቢ.አር.ኤፍ የተሰኘ በሕፃናት እና ታዳጊዎች ዙሪያ የሚሰራ ድርጅት ‘ውባንቺ’ በተባለው ፕሮጀክቱ ስር በማዕከሉ ውስጥ በሚኖሩ ሕፃናት ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ በማመን በክበበፀሃይ ቅጥር ግቢ ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ መካከለኛ ደረጃ ክሊኒክ ገንብቶ ያጠናቀቀ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ክሊኒኩ የታሰበውን አገልግሎት እንዲያቀርብ የሚያስፈልጉት የህክምና መሳሪያዎችና አቅርቦቶች ባለመሟላታቸው ምክንያት እንደታሰበው ሕፃናቱ አግልግሎቱን ማግኘት አልቻሉም።
በመሆኑም ቢ.ቢ.አር.ኤፍ ይህን ችግር ለመቅረፍ ካናዳ ከሚገኝ እና በበጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ተቋቁሞ የህክምና መሳርያዎችን በእርዳታ ከሚያስልክ “ፕሮጀክት ኪዩር” (“Project Cure”) ከተባለ ድርጅት ጋር በመነጋገር ቁሳቁሶቹን የሚላኩበትን ዕድል አመቻችቷል።
ፕሮጀክት ኪዩር ለክበበፀሃይ መካክለኛ ክሊኒክ የ12 ሜትር (40 ፊት) ኮንቴነር የህክምና ቁሳቁስ ልገሳ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ድርጅታችን ስለ እናት በጎ አድራጎት ከክበበፀሐይ ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ ድርጅት ኮንቴይነሩን የማስመጣቱን ሂደት ለማሳካት ኃላፊነቱን ተረክቦ ለዚህ ወጪ የሚያሰፈልገውን የገንዘብ ድጋፍ እያሰባሰበ ይገኛል። የሚሰበሰበውም ገንዘብ ኮንቴነሩን ከካናዳ ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዘ እና ተጨማሪ ቁሳቁሶችን ለማሟላት የሚውል ይሆናል፡፡
ስለሆነም ለዚህ በጎ ሃሳብ ሁላችሁም የበኩላችሁን ድጋፍ እንድርታደርጉ በሕፃናቱ ስም ጥሪ እያስተላለፍን ድጋፋችሁ የሕፃናቱን ደህንነት የተሻለ እንደሚያደርገው እንድትረዱት እንፈልጋለን።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 0 of ETB 2,700,000 0%