በጦርነት ምክንያት ለተጎዱ ወገኖቻችን እንርዳ

cause-image
  • Started by: Esubalew Geletu
  • For: logo.jpg
  • Started on: 09 feb 2022
  • Closing Date: 31 mar 2023

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲዯን የሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ኢትዮጵያ ባጋጠው ጦርነት ምክንያት በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ለሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ አንድነት ገዳም፣ ለሐይቅ እስጢኖስ ምስክር ጉባኤ ቤት፣ ለቦሩ ሜዳ ቅድስት ሥላሴ ጉባኤ ቤት፣ለሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከትና ለደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ከታኅሣሥ 22-27 ቀን 2014 ዓ.ም በተጠቀሱት መካናት በመገኘት 1,800,000 (አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን) ብር የአስቸኳይ የምግብ ነክ ግብዓቶች፣ የጽዳትና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል። ድጋፎቹንም ለብጹዓን አበው፣ ለገዳማቱ አበምኔቶችና የጉባኤ ቤቶቹ መምህራን አስረክቧል፡፡

በቀጣይም ድጋፍ ለሚያሻቸው ወገኖቻችን አሁንም ፈጥነን መድረስ ይቻለን በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ብር) በአውሮፓ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሩ ምእመናን እና በጎ አድራጊዎች 200000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ ማሰባሰብ ይቻለን ዘንድ የበኩልዎትን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 187,647 of ETB 300,000 63%