ቤቶችና ደጆች

project-image
  • Started by: Rose Mestika
  • For: photo_2022-10-20_23-14-47.jpg
  • Started on: 01 feb 2023
  • Closing Date: 29 jun 2024

ምቹ ቤት መልቲ ሚዲያ የሚሰራቸው ስራዎች

1. ቤቶችና ደጆች፣ ለልጄ ምሳ ምን ልቋጥር? የቤተሰብ መድረክ፣ ዓለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንትና ኑ እንተንፍስ የሚባሉ ኩነቶችን ያዘጋጃል
2. በሀገሬ ቴሌቪዥን እና በዩቲዩብ ቻናል በተከታታይ ቤተሰብን የሚያነፁ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል
3. የ24 ሰዓት የኦንላይ ሬዲዮ ለመጀመርም ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ቤቶችና ደጆች የተሰኘው ኩነት አላማው ምንድን ነው?
“ቤቶች እና ደጆች” ቤቶች የምንላቸው ልጆቻቸውን ለማሳደግ ሲሉ ከቅጥር ሥራቸው፣ ከትምህተቸው ውይም ራሳቸው ከፈጠሩት እና ገቢ ከሚያገኙበት ሥራ ወደ ቤታቸው ልጆቻቸውን ለማሳደግ የተመለሱ ማለት ነው፡፡ ደጆች የምንላቸው በቅጥር ሥራ ላይ ወይም በራሰቸው የደጅ ሥራ ላይ ያሉ እና እናት በመሆናቸው የልጅ ማሳደጉን እና የደጁን ሥራ አጣምረው የሚሰሩትን ማለት ነው፡፡
በቤት ውስጥ ሥራ እና በደጅ ሥራ ላይ ያሉ እናቶችን በአንድነት በማሰባሰብ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት፣ ባሉበት ቦታ እንዴት ወጤታማ፣ ጤናማ፣ ስኬታማ እና ብርቱ መሆን እንደሚችሉ ለማሳየት እና ልምዶቻቸውን እንዲለዋወጡ ለማድረግ ታስቦ የሚዘጋጅ ነው፡፡ በተጨማሪም አካል ጉዳተኛ የሆኑ በደጅ ወይም በቤት ውስጥ ሥራ ላይ ያሉ እናቶች ልጆቻቸውን በማሳደግ ሂደት ያሳለፏቸው ተግዳሮቶችንና እንዴት እንዳሳለፏቸው ተሞክሯቸውን የሚያጋሩበት እና የገጠሟቸውን ችግሮች በመንቀስ ለችግሮቹ መፍትሔ የሚፈለግበት ነው፡፡ በተጨማሪም ለቤተሰብ ግንባት አርአያ የሆኑ አባቶችን፣ እናቶችን እና ወጣቶችን እንግዳ አድርገን በመጋበዝ ሌሎች ከተጋባዥ እንግዶች የህይወት ተሞክሮ ተነስተው በራሳቸው፣ በቤተሰባቸው እና በአገራቸው ላይ መልካም ሥራን እንዲሰሩ እና የራሳቸውን ሚና በአግባቡ እንዲወጡ ማነሳሳት ነው፡፡ በስተመጨረሻም የእናቶችን ሸክም በማቅለል ውጤታማ እና ጤናማ እናቶችን ማየት ነው፡፡

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 9,161 of ETB 100,000 9%