የሰሚራን ሕይወት እንታደግ

cause-image
  • Started by: NAJI GEBREMARIAM
  • For: BDO
  • Started on: 17 feb 2022
  • Closing Date: 31 dec 2023

ቤቴል - አዲስ አበባ አካባቢ በእግራቸው መንቀሳቀስ የማይችሉ 10 ጉዳተኛ ወጣት ሴቶችን እንታደግ
ማንኛዋም ሴት ክብር ይገባታል! እርስዎ የሰሚራን የወረደ ህይወት ከፍ በማድረግ አዲስ ህይወትን ሊዘሩ ይችላሉ!
የብሪጅ (ብዴድ) ተልእኮ ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ የጤና እና የትምህርት ድጋፍ እና የስራ እና
የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ በማስቻል የስራ እድል፣ ተነሳሽነት እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው ማብቃት
ነው።
የሰሚራ ህይወት በመገለል ፣በድህነት፤ በሀዘን እና በጭንቀት የተሞላ ነዉ ፡፡
እቺ ልጅ በቆሸሸ እና በጭቃማ ጎዳናዎች ላይ በመዳህና እና በመለመን ስንት ቀናት ፣ ወሮች እና ዓመታት ትገፋለች?
ህይወቷ አሰቃቂ ነዉ፡፡ በደረሰባት የአካል ጉዳት ፣ በማህበራዊ መገለል ፣ የደሀ ደሃ በመሆኗ ፣ በጾታዊ ችግርና ጥቃት
እንዲሁም በመንፈሷ የተጎዳች ነች ፡፡
በዚህ ፕሮጀክት በእርስዎ ድጋፍ በአጠቃላይ ብር 484880.00 ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡
በዚህ ልገሳዎ ለአስር እንደ ሰሚራ አብደላ በጎዳና ላይ በመለመን፤ እንዲሁም ከሰዉ በታች ሆና በመዳህ የተጎዱ ሴቶችን
ህይወት የምንደግፍ ሲሆን በብር 38280.00 ለንጽህና አጠባባቅ የሚያስፈልጋቸዉን እቃዎች ይገዛላቸዋል፤ በብር
127600.00 አነስተኛ ሱቅ በደረቴ እቃዎችን ለመግዛትና ሽጠዉ ከልመና ለማላቀቅ ይረዳቸዋል፤ ብር 319000.00
አስር ዊልቸር በመግዛት ከመንፏቀቅ ጉዞ ወደ አዲስ ጉዞ ከፍ የሚሉበት ይሆናል፡፡ ድጋፍዎ እነዚህ የተጎዱ ሴቶች የኑሮ
ሁኔታ፤ ኢኮኖሚ፤ የጤና ሁኔታ እንዲሁም ማህበራዊ ኑሮን በማሻሻል የህይወት ከፍታን እንደሚጨምር እርግጠኞች
እንሁን፡፡
ድጋፍዎ አፋጣኝ ነዉ፡፡ ምክንያቱም አካለ ስንኩል በመሆኗ፣ አሁን ባለው የኑሮ ችግር ምክንያት ፣ የስነተዋልዶ ጤና
ችግር ስለአለባት፣ በአእምሮ ጭንቀትና እና ተስፋ በመቁረጥ ዉስጥ ስለሆነች ነዉ፡፡
የሰሚራ ዕጣ ፋንታ በእጆዎ ነው ፡፡ ድጋፉ እንደ እርስዎ ባሉ ደጋፊዎች ይሳካል፡፡ እርስዎ የተጎዱ ሴቶችን ሕይወት በመቀየር
ማህበራዊ፤ሀገራዊ፤እና ሀይማኖታዊ ግዴታዎን ስለተወጡ ምሉእና ደስተኛ ነዎት፡፡
እያንዳንዱ አስተዋፅዖ ግብን ለማሳካት ስለሚረዳ ማንኛውንም መጠን ልገሳ እንቀበላለን ፣አሁን ባለው የነሮ ድቀት
እነዚህ ክፍሎች የበለጠ እየቶዱ ነው፡፡ የተጎዱ ሴቶችን ህይወት በመቀየርዎ ደግመን እናመሰግናለን ፡፡
ለሀገራችን ሰላምን እንመኛለን፡፡
ብሪጅ

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 1,250 of ETB 484,880 0%