የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መዋቅርን ከመፍረስ እንታደግ

cause-image
  • Started by: Berhan Gebeyaw
  • For: vectorlogo-800.png
  • Started on: 09 jun 2023
  • Closing Date: 29 dec 2023

"የፈረስውውንም አድሳለሁ፣ እንደቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ።" ት. አሞ 9፣11

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ውስጥ 1482 ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 27 የአንድነት ገዳማት፣ 27 በሰበካ ጉባኤ የሚተዳደሩ ገዳማት፣ 465 አድባራት እና 963 የገጠር አብያተ hርስቲያናት ናቸው። ከነዚህም ውስጥ የጎብኝን ትኩረት የሚስቡ የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ ከ116 በላይ ውቅር፣ ፍልፍልና የዋሻ ውስጥ ኪነ-ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናትና ታሪካዊ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡

በጦርነቱ ምክንያት በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት 183 አብያተ ክርስቲያናት ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን እነዚህን አብያተ ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም የተቋረጡትን መንፈሳዊ አገልግሎቶች እና የልማት ሥራዎች እንደገና ለማስቀጠል የበኩልዎን እገዛ ያድርጉ፤ በረከት ይካፈሉ !

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 152,129 of ETB 5,000,000 3%