Mekdes Children's Horizon

cause-image
  • Started by: Mekdes Horizon
  • For: Mekdes Horizon logo
  • Started on: 27 mar 2024
  • Closing Date: 30 jan 2025

መቅደስ የልጆች አድማስን ለማቋቋም ሃሳቡ የተፀነሰው ከ6 አመታት በፊት ሲሆን በቅን አሳቢዋ አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ የተመሠረተ፣ ሙሉ በሙሉ ሃገር በቀል የሆነ የግብረ ሠናይ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ የተቋቋመው በዋናነት ልዩ ትኩረትና ጥበቃ ለሚያስፈልጋቸው ሕፃናትና ልጆችን ለመደገፍ፣ ከተለመደው የህፃናት ማሳደጊያዎች ለየት ባለ መልኩ የተቋቋመና ትልቅ ኃላፊነትን አንግቦ ትውልድ መቅረፅ ላይ ከፍተኛ ሥራ ለመሥራት ነው።

ማእከሉን ሙሉ ለሙሉ ለመገንባትና በሙሉ አቅሙ ሥራ ለማስጀመር ለማድረግ እስከ 1 ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን በአጠቃላይ በ24 ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ተቋም ነው።

ይህ ድርጅት የመጀመሪያ ማእከሉን የሚገነባውና ሥራውን የሚጀምረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ቀስ በቀስም ወደ ክልሎች ቅርንጫፉን አስፍቶ በመጀመሪያው ዙር 200 ሕፃናትን ከመላው ኢትዮጵያ የሚቀበል ሲሆን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ ደግሞ 1000 ሕፃናት የመቀበል አቅም እንደሚኖረው ይጠበቃል።

50 ሎሚ ለ 50 ሰው ጌጡ ነውና በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በዚህ ግዙፍ ፕሮጀከት በመሳተፍ አናንተም የዚህ በጎ ሥራ ተሳታፊ አንድትሆኑ እና "ከጎናችሁ ነን" እንድትሉን በትህትና እንጠይቃለን።

-----------------------------------

In our minds for some 6 years ago, Mekdes Children's Horizon is now formally established as an Ethiopian Charitable Organisation by the kindhearted artist Mekdes Tsegaye.

Up to 1 billion Birr is needed to fully build the center and bring it to its full capacity.

This organization will build its first center and start its work in Addis Ababa city, gradually expanding into other regions. In the first round, it will accept 200 children from all over Ethiopia.

As the Ethiopian saying goes, "50 lemons are burden for a single person, but beautiful decoration for 50 people", we kindly ask all Ethiopians and friends of Ethiopia all over the world to participate in this huge task and be on our side.

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 2,863 of ETB 10,000,000 0%